ውልና ግላዊነት
አጭሩ ማብራሪያ። ሙሉዎቹ ሰነዶች በድረ ገጹ ላይ ናቸው፤ ሁልጊዜም ወቅታዊዎቹ እነሱ ናቸው።
መተግበሪያውን መጠቀም
መተግበሪያው ለንባብ ነጻ ነው። በአክብሮት ይጠቀሙበት፤ ማንንም ለመጉዳት አይጠቀሙበት።
መለያዎ
መለያው የእርስዎ ነው። በማንኛውም ጊዜ ቁጥርዎን መቀየር ወይም መለያውን ማጥፋት ይችላሉ።
ልገሳ
ልገሳው ዓላማውን ወደ ከፈተው ቤተ ክርስቲያን በቻፓ በኩል ይሄዳል። ክፍያው ከመፈጸሙ በፊት አገልግሎት ክፍያው ይታያል። ልገሳ በመተግበሪያው በኩል አይመለስም።
እዚህ የሚወጣው
ትምህርቶች፣ ዝግጅቶችና ዓላማዎች በተረጋገጡ ደብሮች ይወጣሉ። የማይገባ ነገር ካዩ ያሳውቁ፤ ተቆጣጣሪ ይመለከተዋል።
መረጃዎ
ስልክ ቁጥርዎን፣ መገለጫዎንና የልገሳ መዝገብዎን እንይዛለን። አንሸጥም። ምርጫዎች በአሳሽዎ ላይ ይቀራሉ።